Wednesday, July 15, 2009

What is our Deepest fear?

Thursday, July 16, 2009

(ሰበር ዜና፣ Breaking News) ብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ተጣለ
.fullpost{display:inline;}
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 15/2009)ዛሬ ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ መጣላቸው ተሰማ። የደጀ ሰላም ምንጮች እንደታናገሩት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለፈው ጊዜ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች የብፁዓን አባቶችን መኖሪያ በመደብደብ፣ በር ገንጥሎ በመግባት አደጋ ማድረሳቸው ሲታወቅ ይህ ዜና በተጠናቀረበት ወቅት አባቶች ላይ የደረሰው አደጋ ምን እንደሆነ፣ የተጎዱትስ አባቶች ምን እንደገጠማቸው አልታወቀም። ምንጮቻችን እንደተናገሩት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ሲጮሁና “አድኑኝ” ሲሉ ተሰምተዋል ተብሏል። ፓትርያርኩን በመቃወሙ ዘርፍ ስብሰባዎችን ሲመሩ የሰነበቱት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መኖሪያ በር ከተሰበረ በሁዋላ ብፁዕነታቸው የመኝታ ቤታቸውን በር ቆልፈው ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ማንነታቸውን ለጊዜው ያላወቅነው አንድ አባት ግን ችግር ሳይደርስባቸው አልቀረም። እኚሁ አባት “ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ናቸው፤ ታፍነው ሳይወሰዱ አልቀሩም” ሲሉ ምንጮቻችን ጥቆማ ሰጥተዋል። ይህንኑ ያወቁ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት መግባታቸውም ታውቋል። በሌላም በኩል ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውጪ ቃሊቲ አካባቢ ባለው መኖሪያቸው የሚኖሩት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የጥቃቱ ኢላማ የነበሩ ሲሆን አደጋ ጣዮቹ በራቸውን በተደጋጋሚ ከደበደቡ በሁዋላ፣ በጥበቃ ሠራተኞቻቸው መኖር ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ብፁዕነታቸውም ወደ ፖሊስ ዘንድ በመሄድ ቃላቸውን ሰጥተው ተመልሰዋል።የዛሬው አደጋ ኢላማ የሆኑት አባቶች የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎችና በዛሬው ስብሰባ ላይ ጠንካራ ሐሳብ የሰነዘሩት ናቸው ተብሏል። ነገሩ በርግጥም በተባለው መልኩ ተፈጽሞ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ አደጋ ላይ የመሆኗ የመጨረሻ ምልክት ይሆናል ማለት ነው።ቀሪውን እንደደረሰን እናቀርባለን።ቸር ወሬ ያሰማን፣አሜን
Posted by ደጀ ሰላም

19 አስተያየቶች:
Anonymous said...
I think now it is a time to call our family and friends in Ethiopia to stand together and say STOP to those MAFIAS and Gangsters led by church enemies like.... Let us give a call to Sunday school members that we do know at home country and let them (remind to) stand for their church. Enough is enough. This is just what I can think of right now.We should stand for those fathers who are putting their life at risk for our church. If you (all Dejeselamawiyan) think I am wrong with this idea, let me hear your idea.ZeAklili negne.
July 16, 2009
Anonymous said...
It is really SAD...............
July 16, 2009
orthodoxawit said...
Ere Awetan Amlak ere tadegen ere bekachu bele .Anonymous 1 I agree with you
July 16, 2009
hiwot said...
O God egizo meharene kirstose.Please evrey one pray pray that is the only solution.They better die for truth so that their name will shine for ever in earth & in heaven.O may lady verigin Mary please please give us a true spiritual leader.
July 16, 2009
tade said...
በደምና በስልጣን የሰከረው ካቶሊካዊውን አቡን በቃ ውግድልን የምንልበት ጊዘው አሁን ነው። ለዚህም ለሃይማኖታችን ለመክፈል የምንሳሳው ህይወታችንን ጨምሮ ከቶ ምንም ነገር እንደሌለ ሊያውቁት ይገባል። ምንም እንክዋ እንደለመዱት በጠመንጃና በኃይል የልባቸውን ማድረስ የሚችሉ መስሎዋቸው ከሆነ መቼም መቼም እንደማይሆን ታሪክን መለስ ብለው እንዲያዩ እንመክራቸዋለን። አዎ የጥንት ጠላታችን ካቶሊክ በአጼ ሱዙኒዮስ ዘመን ያደረሰችብንን አደጋ ዛሬም ብትደግመውም እንዳባቶቻችን በመስዋህትነት እንደምናልፈውና ለድል እንደምንበቃ ምንም ጥርጥር የለኝም። ለማንም ግልጽ ሊሆን የሚገባው ነገር እስከዛሬ በቅዱስ ሲኖዶስና በፓትርያርኩ መካከል የነበረው ሽኩቻ በቅድስት በትክርስቲያን እና በካቶሊካዊው ሰርጎ ገብ መካከል መሆኑ ነው። ለዚህም ነው ፓትሪያርኩ ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ ስልጣን እንዳላቸው ለማሳየት የሞከሩት። እግዝአብሄር ቤተክርስቲያንን እና የቤተክርስቲያን የሆኑትን ሁሉ ይጠብቅልን።
July 16, 2009
Anonymous said...
አሁንም ይሄን ውሸታም ብሎግ ታምኑታላችሁ?
July 16, 2009
Anonymous said...
እንዴዴዴዴዴዴዴ………?!!!!! ምን ዓይነት ጉድ ነው የምንሰማው?ቆይ.. አሁን ቀጥታ ወደ ጥያቄዬ ልግባ… ምን ማድረግ ይሻለናል?- ቤተሰቦቻችንን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችን እየተካሄደ ስላለው ነገር ማሳወቅ… ከላይ እንደተባለው በጣም ጥሩ ሃሳብ!- ምናልባት ለመንግሥት ባለሥልጣናት እንደውል ይሆን? ጉዳዩን አጣርቶ የደህንነት ጥበቃ እንዲያደርግና ደብዳቢዎቹን እንዲያጋልጥ?- ወይስ በአቡነ ጳውሎስ ሥር ያሉ አብያተ ክርስቲያናትን በሙሉ boycott እናድርግ? (የለም የለም… ለውሳኔ መፍጠን የለብንም… ጊዜያቸው ደርሶዋል… አብያተ ክርስቲያናቱም አርነት ይወጣሉ!!)- እረ ምን እናድርግ? - አንድ የግድ ማድረግ ያለብን ነገር ግን ይታየኛል፡፡ እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነታችን፡ ጠበቃና መርማሪ ቀጥረንም ቢሆን፡ በመንግሥት ሃይላት ሳንመካ፡ የዛሬውን ጥቃት የሰነዘሩት ሃይላት ማን እንደሆኑ እና ማን እንደላካቸው መመርመር ይኖርብናል፡፡ ከፈለገ 10 ዓመት የፈጀ ጥናትና ምርምርም ይሁን፡ እንዲያውም የተቃጣው አደጋ ረግቦ ሁሉ ነገር አባቶች በፈለጉት መንገድ እየሄደ ቢሆን እንኩዋ፡ የግድ የነዚህ ሃይላት ማንነት፡ ለታሪክ ሲባል መታወቅ አለበት፡፡ የድርድሩ ውጤት ምንም ይሁን ምን፡ የግድ ይህ ፋይል ሳይዘጋ ሊጠና ይገባዋል፡፡ ይህች ባቄላ ያደረች እንደሆን አትቆረጠምም!!! ከዚህ በላይ ምንም ሊመጣ አይችልም!! እባካችሁ እንዳንረሳ ይህን ነገር!!!!! በሃሳቡ ከተስማማን ለጠበቃና ለግል መርማሪ ቅጥር የሚወጣ ወጪ እንኩዋን ካለ እኔም አዋጣለሁ!!! ግድ ነው! ማን መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡ መንግሥትም ከሆነ፡ የካቶሊክ ማፍያም ከሆነ፡ የወይዘሮ እጅጋየሁ ቡድንም ከሆነ፡ ማንም ይሁን ማን…. ጉዳዩ ተጣርቶ፡ ካሳ ሊክስና በአደባባይ ሊናዘዛት ይገባል!!የታባቱንስና! እንዲህ ናትና ድፍረት?!!!የነደደኝ ወይዘሮ
July 16, 2009
Anonymous said...
ሰላም ክርስቲያኖችበጣሙን አሳዛኝ ዜና ሆኖብኛል እባካችሁ ፀልዩ
July 16, 2009
Anonymous said...
እኔ እንደማውቀው የሊቀ ጳጳሳቱ መኖሪያ ሲገባ ከፍተኛ ፍተሻ ያለበትና ውስጡም በፌድራል ፖሊስ እንደሚጠበቅ ነው ። ስለዚህ ይሄ ወሬ ተራ አሉባልታ ይመስለኛል።
July 16, 2009
Anonymous said...
ለውሽቱም ለቅጥፈቱም ከመጸለይ ለቤተክርስቲያን አንድነትት ጸልዩ
July 16, 2009
Anonymous said...
The last anonymousYou might be right but who is security? Probably they are mafiya groups
July 16, 2009
Anonymous said...
የኢትዮጵያ፡ተዋህዶ፡ሕዝበ፡ክርስቲያን፡የደረስንበትን፡የጥፋት፡ጊዜ፡በመረዳት፥ለሃይማኖታችንና፡ለሥርዓተ፡ዕምነታችን፡እስከ፡መጨረሻው፡መስዋዕትነት፡ድረስ፡ለመታገል፡እንዘጋጅ!ርኩሳንን፡ቅዱሳን፡ወብፁዓን፡ከማለት፡እንቆጠብ።እግዚአብሔር፡ቅዱሳኑን፡ያውቃቸዋል፤በጊዜውም፡ለኛም፡ይገልጣቸዋል።ጓዳችንን፡ለማጽዳት፤በሙሉ፡ለብና፤አላንዳች፡ማወላወል፡እንዘጋጅ።ማጅራት፡መቺዎች፡ቤተ፡እግዚአብሔርን፡ደፍረው፡ገብተዋል፡፡ይህች፡ቀንበጥ፡ለምልክት፡ትሁነን።የሮሜና፡የጄኔቫው፡ነጭ፡ለባሽ፡ተንግዲህ፡የማን፡መሆኑን፡እያወቅን፡እንዳላወቅን፡በመሆን፥አምላከ፡ቅዱስ፡እስጢፋኖስን፡በመማጸን፡ተዋህዷዊ፡ፃማችንን፡እንግፋበት።እግዚኦ፡መሓረነ፡ክርስቶስ!በእንተ፡እምነ፡ጽዮን፥ወላዲተ፡አምላክ፥መሓረነ፡ክርስቶስ!ዘደብረ፡ሊባኖስ፡ነኝ።
July 16, 2009
Anonymous said...
betkersetiyane endehone mecheme atetefame atefiwocha yetefalu enjeere gobeze entseleye zeme belachehue lemene temelektalachehu.betekeresetiyanene ye gahaneme dejocheme ayechelatume
July 16, 2009
ያነስኩት said...
አቤቱ አምላክ ሆይ እስከ መቼ ይሆን ካንተ ተለይተን የምንኖረው? መቼ ይሆን ያንተ ብቻ የምታደርገን?እባክህ አምላክ ሆይ ቅረበን…ስለ እናትህ ብለህ ታረቀን! አሜን!
July 16, 2009
Anonymous said...
Let us continue to pray earnestly for all our bishops and our Metropolis. These things matter because—rather than shaking our faith—our love for Christ’s Church compels us to be zealous in maintaining her purity, “without spot or wrinkle or any such thing.”With love in Christ,
July 16, 2009
Anonymous said...
My beloved In Christ,This is not something I usually do, but I am experiencing spiritual distraction from the newspapers I read, the radio stations I listen to or the gossip going around."My zeal has consumed me " Psalm 119:139. I believe the Holy Synod of any Orthodox Church is the highest authority of the Church it is guiding to the truth. It formulates the rules and regulations of the church organization, faith and order of service. It should be chaired by the Patriarch and Bishops who all seek one goal.The leaders of the Church are also good shepherds, as Christ is the good shepherd who gives his life for the sheep. He is the paschal lamb who offered Himself on our behalf. So, the members of the synod, all appointed by the Holy Spirit to lead the Church in the right way, as Christ leads to the truth. The life of the Holy Spirit is in the Church and abides in the Church since the first Pentecost.Today, the division of the bishops in the Ethiopian Orthodox Church leads the flocks to distraction. I guess "for everything there is a season. (Ecc.31)However, we, as Christians, are called to obey the fathers and our responsibility is to pray for the peace of the whole world, the welfare of the Holy Church of God and for the union of all. We must ask the Lord to bring peace to His Church.Let us continue to pray earnestly for all our bishops and our Metropolis. These things matter because—rather than shaking our faith—our love for Christ’s Church compels us to be zealous in maintaining her purity, “without spot or wrinkle or any such thing.”What you and I hear may lead us to confusion and hopelessness. Let us be quick to hear and slow to speak, (James 1"19) In the time of trial we must be strong, along with all faithful Christians because we are one in Christ Jesus. All the Ethiopian church fathers are on trial today. However, it will pass like the wind passes over it. ( Psalm l05:16) Let us pray for them. I believe we have a faith that no one can take away from us. We are sealed by the Holy Spirit. Everything around us is just a distraction.Let us reach out to those Bishops and our spiritual fathers who are around us. The relationship between us and the fathers extends beyond death to the last judgment. Our duty is to obey those who rule over us and be submissive, for they watch over our souls. (Hebrews 12:17) "Fathers, do not provoke your children, lest they become discouraged" (Colossians 3:21). The church fathers' responsibility is to submit themselves to Christ and to feed the life-giving words of God to those who seek them.Let the Metropolitan, Archbishops and Bishops figure out how they can work together for the Holy Church and its salvation. They worked for 17 years in one mind and one soul. They prayed together, celebrated the life-giving divine liturgy. They ate the body and drank the blood of Christ together. They know how good it is and what fire it is. Our duty is to pray for them. We must submit ourselves to one Church, as we submit ourselves to Christ.My brothers and sisters in Christ. Let us pray to the Lord who didst send down His most Holy Spirit upon his apostles at the third hour to set up their next meeting. May He send down upon them a perfect and peaceful love and assistance. Where two or more are gathered, said our Lord, "I will be there." He will be with them and will bless their hard work for his Church. "Great is our Lord, and abundant in power. His understanding is without measure." Psalm 147.May the Lord God remember all of you Orthodox Chrisitians in His kIngdom always, now and ever and unto ages of ages.Amen.
July 16, 2009
Anonymous said...
የምህበረ ቅዱሳን ተንኮል በተ ክርስቲያንን በማፍረስ ሊጠናቀቅ ነውአሁንም የምታደርጉትን ቅሥቀሳ እየተከታተልን ነው ደም ልታፋሥሱ ትፈልጋላችሁ ተው ተው ተው!በታሪክ ተጠያቂዎቹ ማሀበረ ቅዱሳንና አባ ጳውሎስ ናችሁ የማናውቅ መስላችሁ ከጀርባ ተደበቃችሁ የምታደርጉትን እናውቃለንአቡነ ጳውሎስ ቢሞቱ ወይም ሌላ ጳጳስ ቢሞት ቤተ ክርስቲያን ሰላም አይኖራትም እባካችሁ እረፉ;
July 16, 2009
Anonymous said...
ከላይ ዘአክሊሊ እንዳለው የሰ/ት/ቤት ተማሪዎችና ለቤተክርስቲያኑ የሚያስቡ ምዕመናንን ለማስተባበር ይመች ዘንድ ስለወቅታዊ የቤተክርስቲያን ችግር ትክክለኛውን መንስሄና እና የነዚህን የጥፋት መልዕክተኞችን የመጨረሻ ዓላማ በስልክና በኢሜይል እናሳውቅ።እኩይ ተግባራቸውንም ምዕመኑ እንዲያወግዝ ማድረግ።በአዲስ አበባ ያሉ የሁሉም የሰ/ት/ቤት ተማሪዎች የስራ አስፈጣሚ አባላት ተገናኝተው እንዲወያዩና ለአቡነ ጳውሎስ በደብዳቤ አቋሟቸውን ቢገልጡላቸው፣ ግልባጩንም ለሁሉም የአዲስ አበባ አብያተክርስቲያናት አስተዳዳሪዎችና ለቅዱሳን ጳጳሳት ቢየያደርጉ እኔ በጣም እመርጣለሁ። አባቶቻችንም ከጎናቸው እንደሆንን አስበው መንፈሳዊ ብርታት ያገኛሉ ብዬ እገምታለሁ።ዘለዓለም ነኝ
July 16, 2009
Serbelo said...
every body,do you think that 'abune' pawlos is christian? i am 100% shure he has no religion.He is pagan. pray for EOTC
July 16, 2009
Post a Comment

ወዲህ የሚጠቁሙ ገጾች

No comments:

Post a Comment